እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ዘወትር ያስታውስ፤ እነርሱ ራሳቸው ግን ፈጽሞ የተረሱ ይሁኑ።
መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፉ ዘንድ፣ ኀጢአታቸው ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ይኑር።
በጌታ ፊት ሁልጊዜ ይኑሩ፥ መታሰቢያቸውም ከምድረ ገጽ ይጥፋ።
በምድር ላይ የሚያስታውሰው አይኖርም። ዝናውም ከምድር ይጠፋል።
ለስሙ መጠሪያ የሚሆን አንድ ልጅ እንኳ አይቅርለት፤ ከአንድ ትውልድ በኋላ የሚያስታውሰው አይኑር።
ክፉ አድራጊዎችን ግን ይቃወማል፤ መታሰቢያቸውንም ከምድር ላይ ያጠፋል።
ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።
ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፤ በደሌን ሁሉ ደምስስ።
ኃጢአታችንን በፊትህ ታኖራለህ፤ የተሰወረውንም በደላችንን ለአንተ በሚታይ ቦታ ታስቀምጣለህ።
እኔ ጌታ እግዚአብሔርም እናንተን ለሞት አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የእናንተም ስም በእኔ ተመራጮች ዘንድ መራገሚያ ይሆናል፤ ለአገልጋዮቼ ግን የተለየ ስም እሰጣቸዋለሁ።
የቱንም ያኽል በእንዶድና በብዙ ሳሙና ብትታጠቢ፥ በደልሽ ግልጥ ሆኖ ይታየኛል።
ነገር ግን እኔ ይህን ሁሉ ክፋታቸውን እንደማስታውስ ከቶ አይገነዘቡም፤ ከዚህ የተነሣ በገዛ ኃጢአታቸው ተከበዋል፤ ክፉ ሥራቸው ሁሉ ከእኔ የተሰወረ አይደለም።”
ለያዕቆብና ለዘሮቹ መመኪያ የሆነው እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ማለ፦ “እነርሱ የሠሩትን ሥራ ሁሉ አልረሳም።
“ጠላቶቻችን የፈጸሙት በደል በእግዚአብሔር መዝገብ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።