ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው፤ ታማኝነትህም ወደ ጠፈር ይደርሳል።
ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና፤ ታማኝነትህም እስከ ሰማያት ትደርሳለች።
አቤቱ፥ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፥ በሕዝቦችም መካከል እዘምርልሃለሁ፥
በወደድኋቸው ፋንታ አጣሉኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።
ጌታ ሆይ! ስለዚህ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ።
ሰማይ ከምድር ከፍ የሚለውን ያኽል እግዚአብሔር ለሚፈሩት የሚሰጠው ፍቅር ታላቅ ነው።
እግዚአብሔር የመንግሥታት ሁሉ ገዢ ነው፤ ክብሩም ከሰማያት ሁሉ በላይ ነው።
እግዚአብሔር ሆይ፥ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ እስከ ሰማይ፥ እውነተኛነትህም እስከ ደመና ይደርሳል።
ፍቅርና እውነት ይተቃቀፋሉ፤ ጽድቅና ሰላም ይስማማሉ።
ፍቅርህ ለዘለዓለም እንደሚጸናና ታማኝነትህን እንደ ሰማይ እንደሚመሠረት እናገራለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ሰማያት ድንቅ ሥራዎችህን ያመስግኑ የሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤም ታማኝነትህን ከፍ ከፍ ያድርጉ።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ መንገዴ ከመንገዳችሁ፥ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እጅግ ከፍ ያለ ነው።