በሚሄዱበትም ጊዜ በደመና ጋረዳቸው፤ በሌሊትም፥ ብርሃን የሚሰጣቸውን እሳት አዘጋጀላቸው።
ደመናን እንደ መጋረጃ ዘረጋላቸው፤ እሳትም በሌሊት አበራላቸው።
ደመናን ለመሸፈኛ ዘረጋባቸው፥ እሳትንም በሌሊት እንዲያበራላቸው።
በሥራቸውም ረከሰች፥ በጣዖታቸውም አመነዘሩ።
በቀን በደመና ዐምድ መራሃቸው፤ በሌሊትም መንገዳቸውን በእሳት ዐምድ አበራህላቸው።
ምሕረትህም ታላቅ በመሆኑ በዚያ ምድረ በዳ ይጠፉ ዘንድ አልተውካቸውም፤ ነገር ግን የደመናው ዐምድ በቀን ይመራቸው ነበር፤ የእሳቱ ዐምድ በሌሊት ያበራላቸው ነበር።
ቀን በደመና፥ ሌሊት በእሳት ብርሃን መራቸው።
ገና ጎሕ ሳይቀድ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዐምድ ሆኖ የግብጻውያንን ሠራዊት በተመለከተ ጊዜ ሁሉም በፍርሃት ተጨነቁ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር መላውን ከተማና በእዚያም በሚሰበሰቡበት ሁሉ ላይ በቀን ጥቅጥቅ ያለ ደመናን፥ በየሌሊቱም በሚንበለበለው የእሳት ብርሃን ይልካል። የእግዚአብሔርም ክብር ከተማይቱን እንደ ትልቅ ድንኳን ሸፍኖ ይጠብቃታል።
እዚህ ከመድረሳችሁም በፊት እግዚአብሔር በዚያ በረሓ ምን እንዳደረገ ታውቃላችሁ።