በቅዱስ ስሙ ደስ ይበላችሁ! እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው ሁሉ ሐሴት ያድርግ!
በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ።
በቅዱስ ስሙ ክበሩ፥ ጌታን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።
ፍርድን የሚጠብቁ፥ ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው።
ደስታዬ በእርሱ ስለ ሆነ እርሱም በማቀርብለት የተመስጦ ጸሎት ደስ ይበለው።
በሙሉ ልቤ በእግዚአብሔር እመካለሁ፤ ትሑቶች ይህን ሰምተው ደስ ይበላቸው!
አምላክ ሆይ! በአንተ የሚተማመኑትን ሁሉ ስለማትተዋቸው ስምህን የሚያውቁ ሁሉ ይተማመኑብሃል።
እኔ የሚወዱኝን እወዳለሁ፤ የሚፈልጉኝም ያገኙኛል።
ጨለማ በሆነ አገር በድብቅ አልተናገርኩም፤ የያዕቆብን ልጆች፦ ‘ቅርጽ በሌለው ቦታ ፈልጉኝ’ አላልኳቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር እውነቱን እናገራለሁ፤ ትክክል የሆነውንም ነገር እገልጣለሁ።
ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር ድልንና ክብርን ያገኛሉ።
እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠባበቁትና እርሱን ለሚፈልጉ መልካም ነው።
ይህንንም ያደረገው ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ ነው።
እንግዲህ በመጽሐፍ እንደ ተጻፈው “የሚመካ በጌታ ይመካ።”
ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር በሌላ መመካት ከእኔ ይራቅ፤ በዚህም መስቀል ዓለም ከእኔ ተለይቶአል፤ እኔም ከዓለም ተለይቼአለሁ።