መዝሙር 102:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ለዘለዓለም ንጉሥ ነህ፤ ስምህም ከትውልድ ወደ ትውልድ ገናና ሆኖ ይተላለፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፥ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥ እንዲሁ ኀጢአታችንን ከእኛ አራቀ። |
እግዚአብሔርም እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ የአባቶቻችሁ የአብርሃም፥ የይስሐቅ፥ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤ ይህ የዘለዓለም ስሜ ነው፤ በዚህም ስም ከትውልድ እስከ ትውልድ እታወቃለሁ።
የሠራዊት አምላክ፥ የእስራኤል ንጉሥና አዳኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም።
“ከዚህ በፊት የተተውሽና የተጠላሽ ሆነሽ ማንም በአንቺ በኩል የማያልፍ የነበረ ቢሆንም እንኳ፥ የዘለዓለም መመኪያና በየትውልዱ ሁሉ መደሰቻ እንድትሆኚ አደርግሻለሁ።