Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 33:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ዘለዓለማዊ አምላክ መጠጊያህ ዘለዓለማዊ ክንዶቹ ደጋፊዎች ናቸው፤ ጠላትን ከፊትህ ያባርራል፤ እንድትደመስሳቸውም ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ዘላለማዊ አምላክ መኖሪያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከሥርህ ናቸው፤ ‘እርሱን አጥፋው!’ በማለት፣ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 መኖሪያህ የዘለዓለም አምላክ ነው፥ የዘለዓለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፥ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ አጥፋው ይላል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለፊት፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም ክን​ዶች ኀይል ይጋ​ር​ድ​ሃል፤ ጠላ​ት​ህን ከፊ​ትህ አው​ጥቶ፦ አጥ​ፋው ይላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ 2 የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ 2 ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ 2 አጥፋው ይላል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 33:27
48 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ብርቱ በሆነ በያዕቆብ አምላክ ኀይል፥ በእስራኤል እረኛና ጠባቂ ብርታት፥ የእርሱ ቀስት ጽኑ ይሆናል፤ ክንዱም ይበረታል።


“አምላክ ሆይ! የአንተ ዘመን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ስለ ሆነ ዕድሜዬን ሳላጠናቅቅ በግማሽ ዕድሜዬ አትውሰደኝ” አልኩ።


በዙሪያዬ ሁሉ ትገኛለህ፤ በኀይልህም ትጠብቀኛለህ።


እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬና አዳኜ ነው፤ አምላኬ የምጠጋበት አለቴ ነው፤ እርሱ ጋሻዬና የመዳኔ ቀን፥ ጠንካራ መመኪያም ነው።


በችግር ቀን በጥላው ሥር ይደብቀኛል፤ በመቅደሱ ውስጥ ይሰውረኛል፤ በአለትም ላይ ከፍ አድርጎ ይጠብቀኛል።


አምላክ ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው! ሰዎች በአንተ ጥበቃ ሥር ይከለላሉ።


እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤ ችግር በሚደርስብን ጊዜ ሁሉ ረዳታችን ነው።


የሠራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።


የሠራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።


እግዚአብሔር በምሽግዋ ውስጥ ነው፤ እርሱም ከለላዋ መሆኑን አስመስክሮአል።


እነርሱ ስለማይለወጡና አምላክን ስለማይፈሩ ለዘለዓለም በዙፋኑ ላይ ያለው አምላክ የእኔን ጸሎት ሰምቶ ያዋርዳቸዋል።


ግርማው በእስራኤል ላይ፥ ኀይሉም በሰማይ ላይ ስለ ሆነ የአምላክን ኀይል ዐውጁ።


በምሄድበት ቦታ ሁልጊዜ አንተ ኀያል አምባዬ ሁን፤ አንተ ኀያል አምባዬና ምሽጌ ስለ ሆንክ በትእዛዝህ አድነኝ።


በሚጠራኝም ጊዜ እሰማዋለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁም።


አንተ እግዚአብሔርን መከታህ፥ ልዑል አምላክንም ጠባቂህ አድርገሃል።


በጠላቶችህ ላይ ሽብር እልክባቸዋለሁ። አንተም ወደ ፊት ስትሄድ ሒዋውያንን፥ ከነዓናውያንንና ሒታውያንን ከፊትህ አባርራለሁ።


ዛሬ ለእናንተ የምሰጠውን ሕግ ጠብቁ፤ እኔም አሞራውያንን፥ ከነዓናውያንን፥ ሒታውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ሒዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ አባርራለሁ፤


ዐውሎ ነፋስ በሚነሣበት ጊዜ ክፉዎች ተጠርገው ይወሰዳሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን ዘወትር ጸንተው ይኖራሉ።


የእግዚአብሔር ስም እንደ ጠንካራ ምሽግ ነው፤ ስለዚህ ደጋግ ሰዎች ወደ እርሱ ተጠግተው ይድናሉ።


ግራ እጁን ያንተርሰኛል፤ በቀኝ እጁም ያቅፈኛል።


ለድኾች፥ ለመጻተኞችና ለችግረኞች በችግራቸው ጊዜ መጠጊያ ሆነህላቸዋል፤ ከዐውሎ ነፋስ የሚድኑበት ተገንና ከፀሐይ ቃጠሎ የሚጠለሉበት ጥላ ሆነህላቸዋል፤ የጨካኞች ምት የክረምት ወጀብ ግድግዳን እንደሚገፋ ያለ ነው።


ለዘለዓለሙም በእግዚአብሔር ታምናችሁ ኑሩ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም መጠጊያ አምባችን ነውና።


ከእነርሱ እያንዳንዱ ከነፋስ እንደሚከለሉበትና ከወጀብ እንደሚሰወሩበት መጠጊያ ይሆናል፤ በበረሓ እንደሚፈስሱ ጅረቶችና በምድረ በዳ እንደሚገኝ እንደ ትልቅ አለት መጠለያ ይሆናሉ።


ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።


እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን እውነተኛ አምላክ ነህ፤ አንተ ሕያው አምላክ፥ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነህ፤ አንተ በምትቈጣበት ጊዜ ዓለም ይናወጣል፤ የአሕዛብ መንግሥታትም የአንተን ቊጣ ችለው አይቆሙም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በምራታይምና በፈቆድ ሕዝብ ላይ አደጋ ጣሉ፤ ግደሉ፤ አጥፉአቸውም፤ እኔ የማዛችሁን ሁሉ አድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


እጆቻቸውን ይዤ በእግራቸው መረማመድን ያስተማርኳቸው እኔ ነበርኩ፤ ዕቅፍ አድርጌም ይዤአቸው ነበርኩ፤ እነርሱ ግን እኔ እንደምንከባከባቸው አላወቁም።


“አንቺ የወታደር ከተማ ሠራዊትሽን አሰልፊ! ከበባው በእኛ ላይ ተጠናክሮአል፤ የእስራኤልንም መሪ ጒንጩ ላይ በበትር ይመቱታል።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በኤፍራታ ምድር የምትገኚ ቤተልሔም ሆይ! ከይሁዳ ትናንሽ ከተሞች አንድ ብትሆኚም እንኳ ከአንቺ አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ የእስራኤልን ሕዝብ የሚመራ ገዢ ይወጣልኛል።”


እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! አንተ ከጥንት ጀምሮ የነበርክ ቅዱስ ነህ፤ አንተ ስለምትጠብቀን አንሞትም፥ እነርሱ ፍርድህን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መድበሃቸዋል፤ አምባችን ሆይ! እኛን እንዲቀጡ ለእነርሱ ሥልጣን ሰጥተሃቸዋል።


“ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም ሆይ! አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ፥ ወደ አንቺ የተላኩትንም መልእክተኞች በድንጋይ የምትወግሪ፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ፥ እኔም ስንት ጊዜ ልጆችሽን መሰብሰብ ፈለግኹ! አንቺና ሕዝብሽ ግን እምቢ አላችሁ።


ይህን ብታደርጉ የሰላም አምላክ ፈጥኖ ሰይጣንን በእግራችሁ ሥር ይቀጠቅጥላችኋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።


በኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኘውን ሕይወት የሚሰጥ የመንፈስ ቅዱስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶኛል።


እግዚአብሔር አምላክህ እነዚህን ሁሉ ሕዝቦች ለእናንተ አሳልፎ ሲሰጣቸውና እነርሱን ድል በምትነሣበት ጊዜ ሁሉንም መደምሰስ አለብህ፤ ከእነርሱ ጋር ምንም ዐይነት ውል አታድርግ፤ አትራራላቸውም።


ይህንንም የማደርግበት ምክንያት በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴን ጽድቅ ትቼ በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ በክርስቶስ በማመን ለማግኘትና ከእርሱም ጋር ለመሆን ነው።


ስለዚህ ለዘለዓለማዊው ንጉሥ፥ ለማይሞተው፥ ለማይታየው፥ ለአንዱ አምላክ ክብርና ምስጋና ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።


በዘለዓለም መንፈስ አማካይነት ራሱን ነውር የሌለበት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እንድናገለግል ኅሊናችንን ከሞተ ሥራ እንዴት ይበልጥ ያነጻ ይሆን!


እግዚአብሔር ሕዝቦችን እንዲሁም በምድሪቱ የሚኖሩትን አሞራውያንን ሁሉ ከፊታችን አባሮልናል፤ ስለዚህም እርሱ አምላካችን ስለ ሆነ እግዚአብሔርን እናመልካለን።”


እናንተም በመጨረሻው ቀን ለሚገለጠው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል።


እንዳትወድቁ ሊያደርጋችሁና ነቀፋ የሌለባችሁ አድርጎ በደስታ በክብሩ ፊት ሊያቀርባችሁ ለሚችል፥


ያሳታቸው ዲያብሎስ፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት በዲን በሚቃጠል እሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ፤ በዚያም ሌሊትና ቀን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሠቃያሉ።


የእስራኤል ክብር የሆነ እግዚአብሔር አያብልም፤ ሐሳቡንም አይለውጥም፤ እርሱ እንደ ሰው ስላልሆነ ሐሳቡን አይለውጥም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos