ዕውቀት ከጐደላቸው ሰዎች ተለይ! በሕይወትም ትኖራለህ፤ በማስተዋልም መንገድ ወደፊት ተራመድ።”
የአላዋቂነት መንገዳችሁን ተዉ፤ በሕይወት ትኖራላችሁ፤ በማስተዋልም መንገድ ተመላለሱ።”
አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።”
ስንፍናን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በሕይወትም ትኖሩ ዘንድ ዕውቀትን ፈልጉ፥ በመረዳትም ዕውቀትን አቅኑ።”
እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ፤ እኔ የአምላኬን ትእዛዞች መጠበቅ እፈልጋለሁ።
አንቺ ልጄ ሆይ! የምልሽን ስሚ፤ ቃሌንም አድምጪ፤ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።
ተግሣጽን የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ሕይወት መንገድ ያመራሉ፤ ከስሕተታቸው የማይማሩ ሰዎች ግን አደጋ ላይ ይወድቃሉ።
ከጥበበኞች የሚወዳጅ ጥበበኛ ይሆናል። ማስተዋል ከጐደላቸው ሰዎች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን ይጐዳል።
ልጄ ሆይ! አድምጥ፤ ብልኅም ሁን፥ ከእግዚአብሔርም መንገድ ፈቀቅ አትበል፤
የጥበብን መንገድ አሳየሁህ፤ በቀና መንገድም መራሁህ።
እኔን የሚያገኝ፥ ሕይወትን ያገኛል፤ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ያገኛል።
በእኔ አማካይነት ዕድሜህ ይረዝማል፤ ለሕይወትህም ዓመቶች ይጨመራሉ።
በዚያን ጊዜ ሕጌን ይፈጽማሉ፤ ሥርዓቴንም ሁሉ ያከብራሉ፤ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።
እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ ይኖራቸዋል፤ በአንድ መሪ ሥር ተጠቃለው ሕጎቼንና ሥርዓቴን በታማኝነት ይፈጽማሉ።
“በጠባብዋ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ በዚህች በር መግባት የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው፤ ነገር ግን መግባት አይችሉም እላችኋለሁ።
በሌላም በብዙ ቃል እየመሰከረ፥ “በዚህ ጠማማ ትውልድ ላይ ከሚመጣው ቅጣት ራሳችሁን አድኑ!” በማለት መከራቸው።
ደግሞም ጌታ እንዲህ ብሎአል፦ “ከእነርሱ መካከል ተለይታችሁ ውጡ፤ ርኩስ የሆነውንም ነገር አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤
ሌላ ድምፅም ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሕዝቤ ሆይ! በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ፤ የመቅሠፍትዋም ተካፋዮች እንዳትሆኑ፤ ከእርስዋ ውጡ!