ምሳሌ 8:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚወዱኝ ሀብትን እሰጣቸዋለሁ፤ ቤታቸውንም በብልጽግና እሞላዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚወድዱኝ ብልጽግና እሰጣለሁ፤ ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሚወድዱኝ ርስት አወርሳቸው ዘንድ ቤተ መዛግብታቸውንም እሞላ ዘንድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሚወድዱኝ ሀብትን እከፍላቸው ዘንድ ቤተ መዛግብታቸውንም በመልካም ነገር እሞላ ዘንድ። የሚሆነውን ነገር በየቀኑ ብነግራችሁ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ቍጥር አስባለሁ። |
እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን የእርሱ ወራሾች ነን፤ ከክርስቶስም ጋር እንወርሳለን፤ አሁን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች ብንሆን በኋላ የክብሩ ተካፋዮች እንሆናለን።
እናንተ የተሻለና ነዋሪ ሀብት በሰማይ እንዳላችሁ በማወቃችሁ ለእስረኞች ራራችሁላቸው፤ ንብረታችሁም ሲወሰድባችሁ ታግሣችሁ ሁኔታውን በደስታ ተቀበላችሁ።
እርሱ ድኾችን ከትቢያ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ የክብርም ዙፋን ያወርሳቸዋል የምድርን መሠረቶች የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ በእነርሱም ላይ ዓለምን የፈጠረ እርሱ ነው።