ምሳሌ 8:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ ጥበብ፥ ከዕንቊ የምበልጥ ስለ ሆንኩ ምንም ነገር ብትመኙ ከእኔ የሚወዳደር አንድም ነገር የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብ ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናትና፤ ከምትመኙት ነገር ሁሉ አንዳች የሚስተካከላት የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥበብ ከዕንቁ ትበልጣለችና የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍ ጥበብ ትበልጣለችና፥ የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም። |
‘እርሱን ሰምተን እንታዘዘው ዘንድ ከባሕር ማዶ ተሻግሮ ማን ሊያመጣልን ይችላል?’ ብለህ እንዳትጠይቅ፥ እርሱ የሚገኘው ከባሕር ማዶ አይደለም።