Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 20:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዕውቀት የተሞላበት ንግግር፥ ከወርቅና ከከበረ ዕንቊ ይበልጥ የተወደደ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ወርቁም አለ፤ ቀዩም ዕንቍ ተትረፍርፏል፤ ዕውቀት የሚናገሩ ከንፈሮች ግን ብርቅ ጌጦች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቁ ይገኛል፥ የእውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቍ ይገኛል፤ የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 20:15
17 Referencias Cruzadas  

ለማዳመጥ ፈቃደኛ ለሆነ ሰው ብልኅ ሰው የሚሰጠው ተግሣጽ ከወርቅ ጉትቻ ወይም ከጥሩ ወርቅ ከተሠራ ጌጥ ይበልጥ የተወደደ ይሆንለታል።


“እኔ ጥበብ፥ ከዕንቊ የምበልጥ ስለ ሆንኩ ምንም ነገር ብትመኙ ከእኔ የሚወዳደር አንድም ነገር የለም።


መልካም ንግግር እንደ ማር. ወለላ ይጣፍጣል፤ ለሰውነትም ፈውስ የሚሰጥ ነው።


ወርቅን ከማግኘት ጥበብን ማግኘት ይበልጣል፤ ብርንም ከማግኘት ዕውቀትን ማግኘት ይሻላል።


ዕውቀት የሚስፋፋው በብልኆች እንጂ በሞኞች አይደለም።


ከቶ ከአፋችሁ ክፉ ቃል አይውጣ፤ ነገር ግን ለሚሰሙት ደስ የሚያሰኝና ለማነጽ የሚጠቅም ለሰዎችም አስፈላጊ የሆነውን ቃል ተናገሩ።


በአስተሳሰብ መብሰል ጥበበኛነትን ያመለክታል፤ ጣዕም ባለው አነጋገር መናገር ሌሎችን ያስተምራል።


ጥበብ ከውድ ዕንቊ ትከብራለች፤ አንተ ለማግኘት ከምትመኛቸው ነገሮች ሁሉ እርስዋን የሚወዳደራት ከቶ የለም።


ተገቢውን ቃል በተገቢው ቦታ መናገር እጅግ ያስደስታል።


ገዢ ዘወትር መጥፎ ነው እያለ ዕቃን ያራክሳል፤ ገዝቶ ከሄደ በኋላ ግን “በርካሽ ገዛሁ” እያለ ይመካል።


ማንም ሰው ለእንግዳ ሰው ከተዋሰ፥ ልብሱን ውሰድ፤ ለማይታወቀው ሰው መያዣ እንዲሆን አንተ ዘንድ አስቀምጠው።


ይህን ብታደርግ አስተዋይነት ይኖርሃል፤ ንግግርህም ዕውቀት እንዳለህ ይገልጣል፤


ከብር ይልቅ ምክሬን ምረጡ፤ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios