ምሳሌ 8:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አድምጡ! ጥበብ ትጣራለች፤ ማስተዋልም ድምፅዋን ታሰማለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብ ጮኻ አትጣራምን? ማስተዋልስ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ አታሰማምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ጥበብ አትጮኽምን? ማስተዋልስ ድምፅዋን አታሰማምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተስ ጥበብን አስተምር፥ ማስተዋል ትመልስልህ ዘንድ፤ |
“ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፥ ጥርጊያውንም አቅኑ!’ እያለ በበረሓ የሚጮኽ ሰው ድምፅ” ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ስለ ዮሐንስ ነበር።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ፥ በሰማርያ፥ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”