La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 7:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንዲት ሴት በምትኖርበት ቤት አጠገብ ባለው መንገድ ማእዘን ያልፍ ነበር፤ ወደ ቤትዋም አቅጣጫ ይራመድ ነበር፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የቤቷን አቅጣጫ ይዞ፣ በቤቷ ማእዘን አጠገብ ባለው መንገድ ያልፍ ነበር፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በአደባባይ ሲሄድ በቤትዋም አቅራቢያ ሲያልፍ፥ የቤትዋን መንገድ ይዞ ወደ እርሷ አቀና፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በቤቷም አቅራቢያ ባለው መንገድ ሲሄድ ሲናገርም፤

Ver Capítulo



ምሳሌ 7:8
9 Referencias Cruzadas  

እንደዚህች ካለችው ሴት ራቅ፤ ወደ ቤትዋ ደጃፍ እንኳ አትቅረብ።


በየማእዘኑ፥ በየመንገዱና በየገበያ ስፍራ እየቆመች ትጠባበቃለች።


ወደ እርስዋ ቤት የሚወስደው መንገድ ወደ ሞትና ወደ መቃብር የሚያወርድ ጐዳና ነው።


ስለዚህ ከዝሙት ራቁ፤ ሰው የሚያደርገው ሌላው ኃጢአት ሁሉ ከሰውነቱ ውጪ የሚደረግ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ሰው ግን በገዛ ሰውነቱ ላይ ኃጢአት ይሠራል፤


ከወጣትነት ክፉ ምኞት ሽሽ፤ በንጹሕ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ሰዎች ጋር ሆነህ ጽድቅን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ ሰላምን ተከታተል።


አንዳንዶችን ከእሳት አውጥታችሁ አድኑአቸው፤ ለሌሎች በፍርሃት ራሩላቸው፤ ሆኖም በኃጢአት የረከሰውን ሰውነታቸውን የነካውን ልብስ እንኳ ሳይቀር ጥሉ።


አንድ ቀን ሶምሶን የፍልስጥኤማውያን ከተማ ወደሆነችው ወደ ጋዛ ሄደ፤ እዚያም አንዲት አመንዝራ ሴት አይቶ ከእርስዋ ጋር ለማደር ወደ ቤትዋ ገባ፤