ከከርቤ፥ ከእሬትና ከብርጒድ የተቀመመ ሽቶ በንጉሣዊ ልብስህ ላይ ተርከፍክፎአል፤ በዝሆን ጥርስ በተጌጠው ቤተ መንግሥትህም የበገና ሙዚቃ ቃና ያስደስትሃል።
ምሳሌ 7:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከርቤ አልሙንና ቀረፋ ከተባሉት ቅመሞች የተሠራ ሽቶ አርከፍክፌበታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐልጋዬን፣ የከርቤ፣ የአደስና የቀረፋ ሽቱ አርከፍክፌበታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ። |
ከከርቤ፥ ከእሬትና ከብርጒድ የተቀመመ ሽቶ በንጉሣዊ ልብስህ ላይ ተርከፍክፎአል፤ በዝሆን ጥርስ በተጌጠው ቤተ መንግሥትህም የበገና ሙዚቃ ቃና ያስደስትሃል።
በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥ የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች።
“ምርጥ የሆኑ ቅመሞችን፥ ስድስት ኪሎ ግራም ፈሳሽ ከርቤ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን ቀረፋ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን የጠጅ ሣርና፥
በኡዛል የሚኖሩ ዳናውያንና ግሪኮች አሞናውያን ያንቺን ዕቃዎች ለመግዛት የንግድ ስምምነት አደረጉ፤ እነርሱም በአንቺ ሸቀጦች ልዋጭ ቀልጦ የተሠራ ብረት፥ ቅመማ ቅመምና የጠጅ ሣር አቀረቡ።