ምሳሌ 6:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለጌና ክፉ ሰው በየቦታው እየዞረ ነገር እያጣመመ ያወራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናምንቴና ጨካኝ ሰው፣ ነውረኛ አንደበቱን ይዞ የሚዞር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንቱና ክፉ ሰው ጠማማ ንግግር ይዞ ይዞራል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓመፀኛና ሰነፍ የሆነ ሰው ቀና ያልሆኑ መንገዶችን ይሄዳል፤ |
የመጀመሪያው ቅርጫት ከሌሎቹ በፊት ቀደም ብለው የበሰሉ መልካም የበለስ ፍሬዎችን የያዘ ነው፤ ሁለተኛው ቅርጫት ደግሞ ለመብል የማይሆኑ የተበላሹ በለሶችን የያዘ ነው፤
ደግሞም ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን በየሰዉ ቤት እየዞሩ ሰውን የሚያሙ፥ በሰው ነገር የሚገቡና መናገር የማይገባቸውን የሚናገሩ ይሆናሉ።
ስለዚህ ርኲሰትንና የክፋትንም ብዛት ሁሉ አስወግዳችሁ እግዚአብሔር በልባችሁ የተከለውንና ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።
ምላስም እንደ እሳት ናት፤ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ ክፉ ዓለም ናት፤ አካላችንን ትበክላለች፤ ከገሃነም እንደሚወጣ እሳትም የኑሮአችንን ሂደት ሁሉ ታቃጥላለች።
የዳዊት ታላቅ ወንድም ኤሊአብም ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ሰማ፤ እርሱም በዳዊት ላይ በጣም ተቈጥቶ “እዚህ ምን ትሠራለህ? በበረሓ ያሉትንስ እነዚያን ጥቂቶች በጎችህን ለማን ተውካቸው? እኔ ትዕቢተኛነትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ! አሁን የመጣኸው እኮ የጦርነቱን ሁኔታ ለመመልከት ነው!” አለው።