La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 3:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመንገድህ ያለ ፍርሀት ተማምነህ መሄድ ትችላለህ፤ ከቶም አትሰናከልም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም መንገድህን ያለ ሥጋት ትሄዳለህ፤ እግርህም አይሰናከልም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የዚያን ጊዜ መንገድህን ተማምነህ ትሄዳለህ፥ እግርህም አይሰነካከልም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በመንገድህም ሁሉ በመተማመን ትሄዳለህ፥ እግሮችህም አይሰነካከሉም።

Ver Capítulo



ምሳሌ 3:23
13 Referencias Cruzadas  

ሕግህን የሚወዱ ፍጹም የሆነ ሰላም አላቸው፤ ከቶ ምንም ነገር ሊያሰናክላቸው አይችልም።


ጠባቂህ ዘወትር ንቁ ስለ ሆነ እንድትሰናከል አያደርግህም።


ከቤትህ ወጥተህ ስትሄድና ወደ ቤትህም ስትመለስ ዛሬም ለዘለዓለሙ ይጠብቅሃል።


የአምላኩም ሕግ በልቡ ነው፤ እግሩም አይደናቀፍም።


በሁሉም ነገር ታማኝ ሰው ያለ ስጋት ይኖራል። የጠማማ ሰው እርምጃ ግን ይጋለጣል።


የፍትሕን ሂደት ይከታተላል፤ በታማኝነት የሚያገለግሉትንም ይጠብቃል።


በጥበብ ብትራመድ እርምጃህ አይታገድም፤ ብትሮጥም አትሰናከልም።


እነርሱም በጒዞህ ይመሩሃል፤ ስትተኛም ይጠብቁሃል፤ ስትነቃም ያነጋግሩሃል።


በእነርሱ መካከል ደካማና የሚደናቀፍ አይገኝም፤ የሚያንቀላፋና የሚተኛም የለም፤ ትጥቃቸው አይፈታም፤ የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም።


በጥልቁ ሲሄዱ እንዳይሰናከሉ ለጥ ባለ ሜዳ ላይ እንዳለ ፈረስ አደረጋቸው።


እኔ አምላካቸው አበረታቸዋለሁ እነርሱም ለቃሌ ይታዘዛሉ።” እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።