31 የአምላኩም ሕግ በልቡ ነው፤ እግሩም አይደናቀፍም።
31 የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤ አካሄዱም አይወላገድም።
31 የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥ በእርምጃውም አይሰናከልም።
አምላኬ ሆይ! ፈቃድህን መፈጸም እወዳለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው” አልኩ።
ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዞች አትርሳ፤
አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ አኖራለሁ።
እግዚአብሔር በሰው አካሄድ ከተደሰተ የእርምጃውን ትክክለኛነት ያረጋግጥለታል።
እነሆ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤
“እናንተ ትክክለኛውን ነገር የምታውቁና ሕጌ በልባችሁ ያለ ሰዎች አድምጡኝ፤ የሰዎችን ነቀፋ አትፍሩ፤ ወይም በስድባቸው አትደናገጡ።
“እነሆ፥ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን የሚከተለው ነው ይላል ጌታ፤ እኔ ሕጌን በአእምሮአቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
አባቴም እንዲህ እያለ ያስተምረኝ ነበር፤ “ቃሌን በሙሉ ልብህ ያዘው፤ ትእዛዞቼንም ፈጽም፤ በሕይወትም ትኖራለህ።
ጠባቂህ ዘወትር ንቁ ስለ ሆነ እንድትሰናከል አያደርግህም።
ትእዛዝህ መቼም ከአእምሮዬ ስለማይጠፋ፥ ከጠላቶቼ ሁሉ ይልቅ እኔን አስተዋይ ያደርገኛል።
ልባችን ለአንተ እምነተቢስ አልሆነም፤ እግራችንም ከአንተ መንገድ አልወጣም።
እንዲህ ያለው ሰው፥ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፤ ቀንና ሌሊትም ያሰላስለዋል።
እግሮቼ እርሱ በሚወደው መንገድ ይሄዳሉ፤ በማወላወል ወደ ግራም ወደ ቀኝም አልልም።
ሞኝ ሰው የሚነግሩትን ሁሉ አምኖ ይቀበላል፤ ብልኆች ግን እርምጃቸውን በጥንቃቄ ይመረምራሉ።
ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤ ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።
በእኔ በኩል ግን እርምጃዎቼ እየተንገዳገዱ፥ እግሮቼም ሊንሸራተቱ ተቃርበዋል።
መቅዘፊያዎችሽ የተሠሩት ከባሳን በተገኘ የወርካ ዛፍ ነው፤ ወለልሽም የተሠራው ከቆጵሮስ በተገኘ ልዩ በሆነ የጥድ ሳንቃ ነው፤ ዙሪያውም በዝሆን ጥርስ ተለብጦአል።
በትልቁ ጉባኤ ፊት ትክክለኛውን ነገር ተናገርኩ፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ እንደምታውቀው ቃሌን ከመናገር አልቈጥበውም።