በዚያም ለዐይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ፤ ደግሞም በአትክልቱ ቦታ መካከል ሕይወት የሚሰጥ ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት የሚሰጥ ሌላ ዛፍ ነበረ።
ምሳሌ 3:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብ፥ ለሚይዟት ሰዎች ሕይወትን ትሰጣለች፤ እርስዋንም ገንዘብ የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚያቅፏት የሕይወት ዛፍ ናት፤ የሚይዟትም ይባረካሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷ ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት፥ የተመረኰዘባትም ሁሉ ምስጉን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥ የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው። |
በዚያም ለዐይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ፤ ደግሞም በአትክልቱ ቦታ መካከል ሕይወት የሚሰጥ ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት የሚሰጥ ሌላ ዛፍ ነበረ።
እግዚአብሔር አምላክም እንዲህ አለ፦ “እነሆ፥ አዳም ክፉንና ደግን በማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ወስዶ በመብላት ለዘለዓለም እንዲኖር አይገባውም።”
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ‘ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካለው ከሕይወት ዛፍ ፍሬ እንዲበላ አደርገዋለሁ።’
ይህ ወንዝ በከተማይቱ ዋና መንገድ መካከል ሰንጥቆ ያልፋል፤ በወንዙ ግራና ቀኝ በየወሩ እያፈራ በዓመት ዐሥራ ሁለት ጊዜ ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ሕዝቦችን ለመፈወስ ያገለግላሉ።