ምሳሌ 29:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግ ሰው ስለ ድኾች መብት ይቈረቈራል፤ ክፉ ሰው ግን ለእንደዚህ ዐይነቱ ነገር ግድ አይኖረውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቅ ስለ ድኾች ፍትሕ ያውቃል፤ ክፉ ግን ደንታ የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ የድሆችን መብት ይመለከታል፥ ክፉ ሰው ግን ይህንን አያስተውልም። |
እነርሱ እንደ ቅልብ ሰንጋ ወፍረዋል፤ ክፉ ሥራቸውም ገደብ የለሽ ሆኖአል፤ እናትና አባት የሌላቸውን ልጆች መብት አያስከብሩም፤ ለችግረኞችም ትክክለኛ ፍርድ አይፈርዱም።
ወንድሞች ሆይ! ሰው ተሳስቶ አንዳች ጥፋት አድርጎ ቢገኝ መንፈሳውያን የሆናችሁት እናንተ እንዲህ ዐይነቱን ሰው በገርነት አቅኑት፤ ነገር ግን አንተም በዚህ ዐይነት ፈተና እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ።
የናባልን ጉዳይ ከቁም ነገር አታግባው! እርሱ ልክ እንድ አስሙ አጠራር ሞኝ ነው! ጌታዬ፥ የአንተ አገልጋዮች በመጡ ጊዜ እኔ በዚያ አልነበርኩም፤