ልጄ ሆይ! ጠቢብ ብትሆን ደስ ይለኛል፤ ለሚሰድበኝ ሁሉ የምሰጠውም መልስ ይኖረኛል።
ልጄ ሆይ፤ ጠቢብ ሁን፤ ልቤን ደስ አሠኘው፤ ለሚንቁኝ ሁሉ መልስ መስጠት እችል ዘንድ።
ልጄ ሆይ፥ ጠቢብ ሁን፥ ልቤንም ደስ አሰኘው፥ ለሚሰድበኝ መልስ መስጠት ይቻለኝ ዘንድ።
በቃልህ ስለምተማመን ለሚሰድቡኝ ሁሉ መልስ መስጠት እችላለሁ።
እናንተ ነገሥታት አስተውሉ፤ እናንተ የምድር ገዢዎች ተጠንቀቁ።
እነዚህ የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፤ ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።
ብልኅ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን እናቱን ይንቃል።
ሰነፍ፥ በቂ ማስረጃ ከሚሰጡ ከሰባት ሰዎች ይበልጥ አስተዋይ የሆነ ይመስለዋል።
ብልኅ ሰው መከራ ሲመጣ አይቶ ይሸሻል፤ ማስተዋል የጐደለው ሰው ግን ሰተት ብሎ ወደ መከራ ከገባ በኋላ እንደገና ይጸጸታል።
ጥበብን የሚወድ አባቱ ያስደስታል፤ አመንዝሮችን የሚከተል ግን ሀብቱን ያባክናል።
ወንድሜ ሆይ! በአንተ ምክንያት የምእመናን ልብ ስለ ታደሰ ፍቅርህ ታላቅ ደስታንና መጽናናትን ሰጥቶኛል።
ከልጆችሽ አንዳንዶቹ አብ ባዘዘን መሠረት በእውነት ጸንተው በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል።