ሞኝን መልእክተኛ ማድረግ የገዛ እግርን እንደ መቊረጥና ዐመፅን እንደ መጋበዝ ይቈጠራል።
በሞኝ እጅ መልእክትን መላክ፣ የገዛ እግርን እንደ መቍረጥ ወይም መርዝ እንደ መጋት ነው።
በሞኝ አማካኝነት መልእክት የሚልክ፥ እግሮቹን ይቈርጣል፥ ግፍንም ይጠጣል።
ሆምጣጤ ጥርስን፥ ጢስ ዐይንን እንደሚጐዳ ሰነፍ ሰውም ለአሠሪው እንደዚሁ ነው።
ክፉ መልእክተኛ ችግርን ያመጣል፤ ታማኝ መልእክተኛ ግን ሰላምን ያስገኛል።
ቀዝቃዛ ውሃ በሙቀት ጊዜ የሚያረካውን ያኽል ታማኝ መልእክተኛም የላከውን ሰው ያረካል።
ሆኖም ጠቢብ ነኝ ብሎ እንዳይመጣ ሞኝነቱን በመግለጥ መልስለት።
ሞኝ በምሳሌ የሚጠቀመው ሽባ ሰው በአንካሳ እግሮቹ የሚጠቀመውን ያኽል ነው።
ከካሌብ ጋር ሄደው የነበሩት ሰዎች ግን “እኛ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ከቶ ኀይል የለንም፤ በዚያ የሚኖሩት ሰዎች ከእኛ ይበልጥ ብርቱዎች ናቸው” ብለው ተናገሩ።