ምሳሌ 23:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናልባት ሊታዘብህ ስለሚችል የሚያቀርብልህን መልካም ምግብ ተስገብግበህ አትብላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የርሱ ጣፋጭ መብል አያስጐምጅህ፤ ምግቡ አታላይ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጣፋጩ መብል አይመርህ የሐሰት እንጀራ ነውና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብትሳሳ ግን ምግቡን አትውደድ እርሱ የሐሰት እንጀራ ነውና። |
ምግባቸውና የሚጠጡት የወይን ጠጅ ከንጉሡ ማእድ እንዲሆን ታዘዘላቸው፤ በዚህ ዐይነት ለሦስት ዓመት ከሠለጠኑ በኋላ በንጉሡ ፊት ቀርበው የቤተ መንግሥት ሥራቸውን እንዲጀምሩ ተወሰነ።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።