ምሳሌ 23:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ወንበዴ አድብተው ይጠብቁሃል፤ ብዙ ወንዶችን በሕጋዊ ጋብቻ ታማኝ ሆነው እንዳይኖሩ አድርገዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ወንበዴ ታደባለች፤ በሰዎችም መካከል ወስላቶችን ታበዛለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሌባ ታደባለች የእምነተቢሶችንም ቍጥር ታበዛለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እርሷ የሄደ ፈጥኖ ይጠፋል፥ ጠማማ ሰውም ሁሉ ያልቃል። |
ከሞት ይልቅ የመረረ ሌላም ነገር አገኘሁ፤ ይኸውም የሴት ወጥመድነት ነው፤ ሴት እንደ መረብ በሆነ ፍቅርዋ ወንዶችን ታጠምዳለች፤ እንደ እግር ብረት በሆኑ ክንዶችዋም ተጠምጥማ ለመያዝ ትፈልጋለች፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ብቻ ከእርስዋ ሸሽቶ ማምለጥ ይችላል፤ ኃጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።
እስቲ ቀና ብለሽ ወደ ኰረብቶች ራስ ተመልከቺ፤ ከቶ አንቺ ለጣዖቶች ያልሰገድሽበት ስፍራ ይገኛልን? ቀማኛ፥ ሸማቂ፥ ዘላን በበረሓ ተቀምጦ ሊዘርፈው የሚፈልገውን መንገደኛ እንደሚጠባበቅ፥ አንቺም ፍቅረኛዋን ለማጥመድ በየመንገዱ ዳር እንደምትጠባበቅ ሴት ሆነሽ በአምልኮ ዝሙትሽ ኃጢአት ምድርን አረከስሽ።
ከእነርሱ አንዳንዶቹ የዝሙት ኃጢአት እንደ ሠሩ እኛም የዝሙት ኃጢአት እንሥራ፤ እነርሱ ይህን በማድረጋቸው ከእነርሱ ኻያ ሦስት ሺህ ሰዎች በአንድ ቀን ሞተዋል።