ምሳሌ 22:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ እምነት የሌላቸውን ሰዎች ዕቅድ ግን ያስወግዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ የማይታመኑትን ሰዎች ቃል ግን እርሱ ከንቱ ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ዐይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፥ የአታላዩን ቃላት ግን ይገለብጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ ኃጥእ ግን የጥበብን ቃል ይንቃል። |
እግዚአብሔር መላውን ዓለም አተኲሮ በመመልከት፥ በሙሉ ልባቸው በእርሱ ለሚተማመኑት ሁሉ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ እንግዲህ አንተ የሞኝነት ሥራ ስለ ፈጸምክ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይለይህም፤”
ከእግዚአብሔር የመጣ ከሆነ ግን እነርሱን ልታጠፉአቸው አትችሉም፤ እንዲያውም ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ይሆንባችኋል።” እነርሱም የገማልያልን ምክር ተቀበሉ።