Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 22:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ የማይታመኑትን ሰዎች ቃል ግን እርሱ ከንቱ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የጌታ ዐይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፥ የአታላዩን ቃላት ግን ይገለብጣል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ እምነት የሌላቸውን ሰዎች ዕቅድ ግን ያስወግዳል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ ኃጥእ ግን የጥበብን ቃል ይንቃል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 22:12
17 Referencias Cruzadas  

የእግዚአብሔርም ሰው፣ “ሶርያውያን በዚያ ታች ወርደዋልና በዚያ በኩል እንዳታልፍ ተጠንቀቅ” ሲል ለእስራኤል ንጉሥ ላከበት።


በፍጹም ልባቸው የሚታመኑበትን ለማበርታት የእግዚአብሔር ዐይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይመለከታሉና። የሞኝነት ሥራ ስለ ሠራህ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ጦርነት አይለይህም።”


እኛ ግን ወደ አምላካችን ጸለይን፤ ዛቻቸውንም ለመቋቋም ቀንና ሌሊት የሚጠብቁ ዘቦችን መደብን።


ቅኖችን ትክክለኛነታቸው ትመራቸዋለች፤ ወስላቶች ግን በገዛ አታላይነታቸው ይጠፋሉ።


የልብ ንጽሕናን ለሚወድድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።


ሰነፍ፣ “አንበሳ በውጭ አለ፤ በጐዳና ላይ እገደላለሁ” ይላል።


ከእግዚአብሔር ከሆነ ግን ልትገቷቸው አትችሉም፤ እንዲያውም ከእግዚአብሔር ጋራ ስትጣሉ ትገኙ ይሆናል።”


ከዚያም በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚያስወግደውና በምጽአቱም ክብር ፈጽሞ የሚያጠፋው ዐመፀኛ ይገለጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos