እኔም እንዲህ ስል ጸለይሁ፤ “አምላክ ሆይ! እንዴት እንደሚሳለቁብን ተመልከት፤ ይህም ስድባቸው በራሳቸው ላይ ይምጣባቸው፤ ያላቸውን ሀብት ሁሉ ተገፈው በባዕድ አገር ስደተኞች ይሁኑ፤
ምሳሌ 18:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአትና ውርደት የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው፤ ክብርህን ብታጣ በምትኩ የምታገኘው ውርደት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤ ከዕፍረትም ጋራ ውርደት ትመጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀጥእ በመጣ ጊዜ ንቀት ደግሞ ይመጣል፥ ነውርም ከስድብ ጋር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአተኛ ወደ ጥፋት ጥልቅ በመጣ ጊዜ ቸል ይላል፥ ውርደትና ሽሙጥም በላዩ ይመጣል። |
እኔም እንዲህ ስል ጸለይሁ፤ “አምላክ ሆይ! እንዴት እንደሚሳለቁብን ተመልከት፤ ይህም ስድባቸው በራሳቸው ላይ ይምጣባቸው፤ ያላቸውን ሀብት ሁሉ ተገፈው በባዕድ አገር ስደተኞች ይሁኑ፤
ስድብ ልቤን ስለ ሰበረው ተስፋ ቈረጥኩ፤ የሚያስተዛዝነኝ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንም አልነበረም፤ የሚያጽናናኝ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንም አልተገኘም።
የሳኦልም ቊጣ በዮናታን ላይ ነድዶ እንዲህ አለ፤ “አንተ የጠማማና የዐመፀኛ ሴት ልጅ! በራስህ ላይ ኀፍረትንና በእናትህም ላይ ውርደትን ለማምጣት ከእሴይ ልጅ ጋር መወዳጀትህን ደኅና አድርጌ ዐውቃለሁ!