ምሳሌ 18:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳያዳምጡ መልስ መስጠት፥ ሞኝ ያደርጋል፤ አሳፋሪም ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማዳመጡ አስቀድሞ የሚመልስ፣ ቂልነትና ዕፍረት ይሆንበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳይሰማ ነገርን የሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል። |
ንጉሡም ጺባን “የመፊቦሼት የነበረው ንብረት ሁሉ ከእንግዲህ የአንተ ነው” አለው። ጺባም “ንጉሥ ሆይ! እነሆ እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ ዘወትር አንተን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ለመሥራት እተጋለሁ!” ሲል መለሰ።
ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ፤ ዳንኤልንም ለማዳን ወሰነ፤ ፀሐይም እስክትጠልቅ ድረስ እርሱን ለማዳን የሚችልበትን ዘዴ ሁሉ ለማግኘት ሞከረ።