ምሳሌ 17:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ክፉ ነገርን ይሰማሉ፤ ሐሰተኞችም ሐሰትን ያዳምጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኩይ ሰው ክፉ ንግግር ያዳምጣል፤ ሐሰተኛም የተንኰለኛን አንደበት በጥንቃቄ ይሰማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ሰው የበደለኛን ከንፈር ይሰማል፥ ሐሰተኛም ወደ ተንኰለኛ ምላስ ያደምጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ ሰው ከሕግ ውጭ የሆኑትን ሰዎች አንደበት ይሰማል፤ ጻድቅ ግን የሐሰት ከንፈሮችን አይመለከትም። ለሚያምን በዓለም ያለው ገንዘቡ ነው፥ ለማያምን ግን መሐለቅ የለውም፥ |
ነቢያትንም አፋቸውን ለማስያዝ እንዲህ ይሉአቸዋል፦ ‘ቀጥተኛ የሆነውን ነገር አትንገሩን፤ እኛ ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ንገሩን፤ ለስላሳና ማረሳሻ የሆነውን ነገር አስተምሩን።
ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?”