Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 17:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እኩይ ሰው ክፉ ንግግር ያዳምጣል፤ ሐሰተኛም የተንኰለኛን አንደበት በጥንቃቄ ይሰማል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ክፉ ሰው የበደለኛን ከንፈር ይሰማል፥ ሐሰተኛም ወደ ተንኰለኛ ምላስ ያደምጣል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ክፉ ሰዎች ክፉ ነገርን ይሰማሉ፤ ሐሰተኞችም ሐሰትን ያዳምጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ክፉ ሰው ከሕግ ውጭ የሆኑትን ሰዎች አንደበት ይሰማል፤ ጻድቅ ግን የሐሰት ከንፈሮችን አይመለከትም። ለሚያምን በዓለም ያለው ገንዘቡ ነው፥ ለማያምን ግን መሐለቅ የለውም፥

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 17:4
10 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ለክፉዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤ በጠማሞችም እጅ ጣለኝ።


አላዋቂው ሰው ሁሉን ያምናል፤ አስተዋይ ግን ርምጃውን ያስተውላል።


ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል።


ባለራእዮችን፣ “ከእንግዲህ ራእይን አትዩ!” ይላሉ፤ ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፤ “እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን፤ ደስ የሚያሠኘውን ንገሩን፤ የሚያማልለውን ተንብዩልን።


ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?”


እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ የሚናገሩት እንደ ዓለም ነው፤ ዓለምም ይሰማቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos