አባትህ ዳዊትና ተከታዮቹ ብርቱ ጦረኞች እንደሆኑና ግልገሎችዋ እንደ ተነጠቁባትም ድብ አስፈሪዎች መሆናቸውን ታውቃለህ፤ አባትህ በጦር ልምድ የተፈተነ ወታደር በመሆኑ ሌሊቱን ከሠራዊቱ ጋር አያድርም፤
ምሳሌ 17:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝን የሞኝነት ሥራ ሲሠራ ከመገናኘት ይልቅ ልጆችዋ የተነጠቁባትን ድብ መገናኘት ይሻላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝን በቂልነቱ ከመገናኘት፣ ግልገሎቿን የተነጠቀችን ድብ መጋፈጥ ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰነፍን በስንፍናው ከመገናኘት ልጆችዋ የተነጠቁባትን ድብ መገናኘት ይሻላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐዋቂ ሰው በትካዜ ውስጥ ይወድቃል፥ አላዋቂዎች ግን ክፉን ያስባሉ። |
አባትህ ዳዊትና ተከታዮቹ ብርቱ ጦረኞች እንደሆኑና ግልገሎችዋ እንደ ተነጠቁባትም ድብ አስፈሪዎች መሆናቸውን ታውቃለህ፤ አባትህ በጦር ልምድ የተፈተነ ወታደር በመሆኑ ሌሊቱን ከሠራዊቱ ጋር አያድርም፤
ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው።
ግልገሎችዋ የተወሰዱባት ድብ እንደምታደርግ እኔም አደጋ እጥልባችኋለሁ፤ እቦጫጭቃችሁማለሁ፤ እንደሚባላ አንበሳ እሆንባችኋለሁ፤ እንደሚበጣጥስ ክፉ አውሬም እበጣጥሳችኋለሁ።
ከዚያ በኋላ ሄሮድስ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎቹ እንዳታለሉት በተገነዘበ ጊዜ፥ በጣም ተቈጣ፤ ወደ ቤተልሔምና በዙሪያዋም ወዳሉት መንደሮች ሁሉ ወታደሮቹን ልኮ፥ ከከዋክብት ተመራማሪዎቹ በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ዕድሜአቸው ሁለት ዓመት የሆናቸውንና ከዚያ በታች የሆኑትን በቤተልሔምና በአካባቢው የነበሩትን ወንዶች ሕፃናትን አስገደለ።