Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 17:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሞኝን በቂልነቱ ከመገናኘት፣ ግልገሎቿን የተነጠቀችን ድብ መጋፈጥ ይሻላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰነፍን በስንፍናው ከመገናኘት ልጆችዋ የተነጠቁባትን ድብ መገናኘት ይሻላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሞኝን የሞኝነት ሥራ ሲሠራ ከመገናኘት ይልቅ ልጆችዋ የተነጠቁባትን ድብ መገናኘት ይሻላል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዐዋቂ ሰው በትካዜ ውስጥ ይወድቃል፥ አላዋቂዎች ግን ክፉን ያስባሉ።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 17:12
8 Referencias Cruzadas  

አባትህና ሰዎቹ የማይበገሩ ተዋጊዎችና ግልገሎቿ እንደ ተነጠቁባት የዱር ድብ አስፈሪ መሆናቸውን አንተም ታውቃለህ፤ በተጨማሪም አባትህ በቂ ልምድ ያለው ነው፤ ሌሊቱን ከሰራዊቱ ጋራ አያድርም፤


ኤልሳዕም ዘወር ብሎ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ ከዚያም ሁለት እንስት ድቦች ከዱር ወጥተው ከልጆቹ አርባ ሁለቱን ሰባበሯቸው።


ክፉ ሰው ዐመፅን ብቻ ይፈልጋል፤ በርሱም ላይ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።


ድንጋይ ይከብዳል፤ አሸዋም ሸክም ነው፤ የቂል ሰው ቍጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።


ታዳጊ በሌለው ሕዝብ ላይ የተሾመ ጨካኝ ገዥ፣ እንደሚያገሣ አንበሳ ወይም ተንደርድሮ እንደሚይዝ ድብ ነው።


ጠቢብ ሰው ከቂል ጋራ ወደ ሸንጎ ቢሄድ፣ ቂሉ ይቈጣል፤ ያፌዛል፤ ሰላምም አይኖርም።


ግልገሎቿን እንደ ተነጠቀች ድብ፣ እመታቸዋለሁ፤ እዘነጣጥላቸዋለሁ። እንደ አንበሳም ሰልቅጬ እውጣቸዋለሁ፤ የዱር አራዊትም ይገነጣጥላቸዋል።


ሄሮድስ ጠቢባኑ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ በጣም ተናደደ። ከጠቢባኑ በተነገረው መሠረት፣ ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን የቤተ ልሔምንና የአካባቢዋን መንደሮች ወንድ ልጆች ሁሉ ልኮ አስገደለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos