ጥልና ክርክር በበዛበት ቤት በታላቅ ግብዣ ላይ ከመገኘት ይልቅ ሰላም ባለበት ቤት ደረቅ የዳቦ ቊራሽ መመገብ ይሻላል።
ጠብ እያለ ግብዣ ከሞላበት ቤት ይልቅ፣ በሰላምና በጸጥታ ድርቆሽ ይሻላል።
ጥል ባለበት ዘንድ ግብዣ ከሞላበት ቤት ይልቅ በጸጥታ ደረቅ ቁራሽ ይሻላል።
ብዙ ደስታ ከሞላበትና ከክርክር ጋር የዐመፃ ፍሪዳ ካለበት ቤት ይልቅ፥ ከሰላም ጋር ደረቅ ቍራሽ ይሻላል።
ከክፉ ሰው ብዙ ሀብት ይልቅ፥ የደግ ሰው ጥቂት ሀብት ይበልጣል።
ሀብታም ሆኖ በሁከት ከመኖር ድኻ ሆኖ እግዚአብሔርን በማክበር መኖር ይሻላል።
ጥላቻ ባለበት ስፍራ ጮማ ሥጋ ከመብላት ፍቅር ባለበት ስፍራ ጎመን መብላት ይሻላል።
ፍትሕን በማጓደል ከሚገኝ ብዙ ሀብት ይልቅ በእውነት የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል።
የጌታው ልጅ ወራዳ ከሆነ ብልኅ አገልጋይ በጌታው ልጅ ላይ የበላይነት ይኖረዋል፤ ከወንድማማቾቹም ጋር ርስት ተካፋይ ይሆናል።
ከጨቅጫቃና ከነዝናዛ ሚስት ጋር አብሮ ከመኖር በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።
ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር ይልቅ በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።
“እኔ መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ የስእለቴን መባ አቅርቤአለሁ፤