ምሳሌ 15:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጠቢባን አንደበት ዕውቀትን ያፈልቃል። የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ይለፈልፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠቢብ አንደበት ዕውቀትን ታወድሳለች፤ የሞኞች አንደበት ግን ቂልነትን ያፈልቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠቢባን ምላስ እውቀትን ያሳምራል፥ የሰነፎች አፍ ግን ስንፍናን ያፈልቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠቢባን ምላስ መልካም ነገርን ታውቃለች፤ የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል። |
ደካሞችን በቃል ማጽናትን ዐውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የምሁርን አንደበት ሰጥቶኛል፤ በየማለዳው ከእንቅልፍ ያነቃኛል፤ እንደ ተማሪም አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ይከፍታል።