La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 15:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፌዘኛ ተግሣጽን አይወድም፤ ከጠቢባንም ምክርን አይጠይቅም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፌዘኛ መታረምን አይወድድም፤ ጠቢባንንም አያማክርም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፌዘኛ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ወደ ጠቢባንም አይሄድም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አላዋቂ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ከጠቢባንም ጋር አይነጋገርም።

Ver Capítulo



ምሳሌ 15:12
11 Referencias Cruzadas  

አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ ተብሎ የሚጠራ ሌላም ነቢይ አለ፤ ነገር ግን እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል ስለማይናገር እርሱን አልወደውም” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “አንተ ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።


“ይህም ሆኖ ሳለ እግዚአብሔርን ‘ከእኛ ራቅ፤ የአንተን መንገድ ማወቅ አንፈልግም’ ይሉታል።


“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!


ብልኅ ልጅ የአባቱን ምክር ይቀበላል፤ ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም።


ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል፤ አያገኛትም። አስተዋዮች ግን ዕውቀትን በቀላሉ ይገበያሉ።


ትክክለኛውን መንገድ ትቶ ስሕተት የሆነ ነገር የሚያደርግ ይቀጣል፤ ተግሣጽንም የሚጠላ ይጠፋል።


እናንተ በፍርድ አደባባይ የሚገሥጻችሁን ጠላችሁ፤ እውነት የሚናገረውንም ተጸየፋችሁ።


ዓለም እናንተን ሊጠላ አይችልም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ መሆኑን ስለምመሰክርበት እኔን ይጠላኛል።


ሰዎች ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት ለመስማት የማይፈልጉበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን ለወሬ በመጐምጀት እነርሱ ራሳቸው የሚወዱትን ነገር የሚነግሩአቸውን አስተማሪዎች ይሰበስባሉ።