ምሳሌ 13:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለ ድካም በቀላሉ የተገኘ ሀብት ወዲያው ይጠፋል፤ ተግቶ በመሥራት የተገኘ ሀብት ግን እየበዛ ይሄዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያላግባብ የተገኘ ገንዘብ እየተመናመነ ያልቃል፤ ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት የሚያከማች ግን ይጠራቀምለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፥ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀጢአት በችኮላ የሚገኝ ሀብት ይጐድላል፥ በእውነት ለራሱ የሚሰበስብ ግን ይበዛለታል። ጻድቅ ይራራል፥ ያበድራልም። |
ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ሀብትን የሚሰበስብ፥ ያልጣለችውን ዕንቊላል ታቅፋ እንደምትፈለፍል ቆቅ ነው፤ በዕድሜው አጋማሽ የሰበሰበውን ሃብት ሁሉ ያጣል። በመጨረሻም ሞኝነቱ ግልጥ ይሆናል።