ምሳሌ 11:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋውም አብሮት ይሞታል፤ በኀይሉ መመካቱም አብሮት ይጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው ከንቱ ትሆናለች፤ በኀይሉ የተመካበትም ሁሉ እንዳልነበረ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋው ይቈረጣል፥ የኃያል አለኝታም ይጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቅ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋውን አያጣም፥ የክፉዎች ትምክሕታቸው ግን ትጠፋለች። |
ታዲያ ሊገድሉህ በሚመጡበት ጊዜ አሁንም ራስህን እንደ አምላክ ትቈጥር ይሆን? በገዳዮችህ እጅ ወድቀህ ስትገኝ ሰው እንጂ አምላክ ያለመሆንህ ይታወቃል።