የሳዶቅ ዘር የሆነው ሊቀ ካህናት ዐዛርያስም ንጉሡን፥ “ሕዝቡ ዐሥራቱን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማምጣት ከጀመረ ወዲህ፥ እነሆ፥ በቂ ምግብ አለን፤ ብዙም ተርፎናል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለ ባረከ እነሆ፥ ይህን ሁሉ በብዛት አግኝተናል” አለው።
ምሳሌ 11:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንድ ሰዎች በለጋሥነት ገንዘባቸውን ይበትናሉ፤ ነገር ግን ሀብታቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ሌሎች ደግሞ ያለ ልክ ለገንዘባቸው ይሳሳሉ፤ ነገር ግን ድኽነታቸው እየበዛ ይሄዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዱ በለጋስነት ይሰጣል፤ ሆኖም ይበልጥ ያገኛል፤ ሌላው ያለ መጠን ይሰስታል፤ ግን ይደኸያል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልግስና የሚሰጥ ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፥ ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የየራሳቸውን የሚዘሩና የሚያበዙ አሉ፤ እየሰበሰቡ የሚያጐድሉም አሉ። |
የሳዶቅ ዘር የሆነው ሊቀ ካህናት ዐዛርያስም ንጉሡን፥ “ሕዝቡ ዐሥራቱን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማምጣት ከጀመረ ወዲህ፥ እነሆ፥ በቂ ምግብ አለን፤ ብዙም ተርፎናል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለ ባረከ እነሆ፥ ይህን ሁሉ በብዛት አግኝተናል” አለው።
አንዳንድ ሰዎች ምንም ሳይኖራቸው ሀብታም መስለው ለመታየት ይጥራሉ፤ ሌሎች ደግሞ ብዙ ሀብት እያላቸው፥ ምንም ሀብት እንደሌላቸው መስለው ይኖራሉ።
እነሆ ብዙ ዘርታችሁ ጥቂት ሰበሰባችሁ፤ ትበላላችሁ፤ ነገር ግን አትጠግቡም፤ ትጠጣላችሁ፤ ነገር ግን አትረኩም፤ ደራርባችሁ ትለብሳላችሁ፤ ነገር ግን አይሞቃችሁም፤ ሠርታችሁ የምታገኙት ደመወዝ ስለማይበረክትላችሁ፥ በቀዳዳ ኪስ ውስጥ የማኖር ያኽል ይሆናል።
ሰው የእግዚአብሔርን ሀብት ይዘርፋልን? ሆኖም እናንተ እኔን ዘርፋችኋል፥ እናንተ ግን እንዴት ከአንተ እንዘርፋለን ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ ከእኔ የዘረፋችሁት ዐሥራትንና መባን ባለመክፈላችሁ ነው።
ስጡ፤ ለእናንተም ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ እንዲሁ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም በጥሩ መስፈሪያ ታምቆና ተጠቅጥቆ እስኪትረፈረፍ ድረስ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል።”