ምሳሌ 10:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች ዘወትር ከስፍራቸው አይነቃነቁም፤ ክፉዎች ግን በምድር ላይ አይኖሩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቃን ፈጽሞ አይነቀሉም፤ ክፉዎች ግን በምድር አይኖሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ ለዘለዓለም አይናወጥም፥ ክፉዎች ግን በምድር ላይ አይቀመጡም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃን ለዘለዓለም አይናወጡም፤ ኃጥኣን ግን በምድር ላይ አይቀመጡም። |
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም። በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።
እነርሱም “የእነዚህን ክፉ ሰዎች ፍጻሜ የከፋ ያደርገዋል። የወይኑንም ተክል ቦታ ፍሬውን በየጊዜው ለሚሰጡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት።