ምሳሌ 10:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን ከለላ ነው፤ ለክፉ አድራጊዎች ግን መጥፊያቸው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን መጠጊያ፣ ክፉ ለሚያደርጉ ግን መጥፊያቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ መንገድ ያለ ነውር ለሚሄድ አምባ ነው፥ ክፋትን ለሚያደርጉ ግን ጥፋት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን መፍራት ለደግ ሰው ብርታት ነው፥ ጥፋት ግን ክፋት ለሚያደርጉ ነው። |
ጥበብ ያላቸው እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፤ አስተዋዮችም ያውቋቸዋል፤ የእግዚአብሔር መንገድ ትክክል ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ኃጢአተኞች ግን ይሰናከሉበታል።