ምሳሌዎቹም ጥበብንና መልካም ምክርን ለመገንዘብ፥ ጥልቅ አስተሳሰብ ያለውን የዕውቀት ቃል ለመረዳት የሚጠቅሙ ናቸው።
ጥበብንና ተግሣጽን ለመቀበል፤ ጥልቅ ሐሳብ የሚገልጡ ቃላትን ለማስተዋል፤
ጥበብንና ተግሣጽን ለማወቅ፥ የእውቀትንም ቃል ለማስተዋል፥
ጥበብንና ተግሣጽን ለማወቅ፥ የጥበብንም ቃል ለማወቅ፥
እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብን የሚሰጥ ትምህርት ነው፤ ክብርን ለማግኘት በቅድሚያ ትሑት መሆን ያስፈልጋል።
ወርቅን ከማግኘት ጥበብን ማግኘት ይበልጣል፤ ብርንም ከማግኘት ዕውቀትን ማግኘት ይሻላል።
ሞኝ የተፈጥሮ ማስተዋል ስለሌለው ገንዘቡን ጥበብን ለማግኘት ቢያውል ምንም አይጠቅመውም።
ምክርን ብትሰማና ለመማርም ፈቃደኛ ብትሆን የኋላ ኋላ ጥበብ መገብየትህ አይቀርም።
እኔ የምልህን ሁሉ ብትሰማ፥ ቀጥተኛ፥ ትክክልና ቅን የሆነውን መንገድ ትገነዘባለህ፤ ልታደርገው የሚገባህንም መልካም ነገር ሁሉ ታውቃለህ።
ልጆቼ ሆይ! የአባታችሁን ምክር ስሙ፤ በጥንቃቄ አዳምጡ፤ ማስተዋልንም ታገኛላችሁ።
ጥበብን እንደ እኅትህ፥ ማስተዋልንም እንደ ቅርብ ወዳጅህ አድርገህ ቊጠራቸው።
የምትማሩትን አስተውሉ፤ ብልኆች ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት።
እናንተ ዕውቀት የሌላችሁ፥ ዕውቀትን ለመገብየት ተማሩ፤ እናንተ ሞኞች፥ ማስተዋልን ገንዘብ አድርጉ።