ምሳሌ 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልትይዘው የምትፈልገው ወፍ እያየህ የምታጠምደው ወጥመድ ዋጋ የለውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወፎች ፊት እያዩ ወጥመድ መዘርጋት፣ ምንኛ ከንቱ ነው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጥመድ በወፎች ዐይን ፊት በከንቱ ይተከላልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወጥመድን ለወፎች በከንቱ የሚያጠምዱ አይደለምና፥ |
ፍላጻም ሆድ ዕቃውን እንደሚወጋው ዐይነት ሆነ፤ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ ወፍ መሰለ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕይወቱ በአደጋ ላይ ለመውደቅ መቃረቡን አላወቀም።
ሽመላዎች እንኳ የሚመለሱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ ዋኖሶች፥ ጨረባዎች፥ ዋርዳዎችም በኅብረት የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ እናንተ ሕዝቤ ግን እንድትተዳደሩበት የሰጠኋችሁን ሕግ አታውቁም።