Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 1:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ይህን የሚያደርጉ ሰዎች የሚሞቱበትን ወጥመድ ራሳቸው ይዘረጋሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እነዚህ ሰዎች የሚያደቡት በገዛ ደማቸው ላይ ነው፤ የሚሸምቁትም በራሳቸው ላይ ብቻ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እነርሱም በደማቸው ላይ ያደባሉ፥ በነፍሳቸውም ላይ ይሸምቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 መግደልን የለመዱ እነርሱ ክፋትን ለራሳቸው ይሰበስባሉ። የኀጢአተኞች ሰዎች አወዳደቃቸው ክፉ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 1:18
13 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ሃማን መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው እንጨት ላይ ተሰቀለ፤ ከዚያም በኋላ የንጉሡ ቊጣ በረደ።


አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።


እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ።


ምናልባትም እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ከበደል ንጹሕ የሆነውን ሰው መንገድ ላይ አድብተን እንድንገድለው ከእኛ ጋር ና!


ልትይዘው የምትፈልገው ወፍ እያየህ የምታጠምደው ወጥመድ ዋጋ የለውም።


መልካም ሥራ ለመሥራት ቊርጥ ውሳኔ ያደረገ ሰው በሕይወት ይኖራል፤ ስሕተት በማድረግ የሚጸና ግን ይሞታል።


ደግነት የመልካሙን ሰው ኑሮ ያቃናለታል፤ ክፉ ሰው ግን በገዛ ክፋቱ ይወድቃል።


አንድ ሰው የሰውን ሕይወት ቢያጠፋ እስኪሞት ድረስ እየሸሸ ይኑር፤ ማንም ሰው አያስጠጋው።


እንግዲህ አንተ ንስሓ ባለመግባትህና እልኸኛ በመሆንህ የእግዚአብሔር ቊጣና ትክክለኛ ፍርድ በሚገለጥበት ቀን ቅጣትህ እንዲበዛ ታደርጋለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos