‘ጳውሎስ ሆይ! አትፍራ! በሮም ንጉሠ ነገሥት ፊት መቆም ይገባሃል! እነሆ፥ ከአንተ ጋር የሚጓዙትንም ሁሉ እግዚአብሔር ለአንተ ብሎ ከሞት ያድናቸዋል’ ብሎ ነግሮኛል።
ፊልሞና 1:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያውም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ሰምቶ ወደ እናንተ እንድመጣ እንደሚያደርገኝ ተስፋ ስላለኝ የማርፍበትን ቤት አዘጋጅልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም ሌላ፣ ጸሎታችሁ መልስ አግኝቶ ወደ እናንተ ለመምጣት ተስፋ ስለማደርግ ማረፊያ አዘጋጁልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞ ከዚህም ጋር የማስተናገጃ ቤት አዘጋጅልኝ፤ በጸሎታችሁ ለእናንተ እንደምሰጥ ተስፋ አደርጋለሁና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ ከዚህም ጋር የማስተናገጃ ቤት አዘጋጅልኝ፤ በጸሎታችሁ ለእናንተ እንድሰጥ ተስፋ አደርጋለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ ከዚህም ጋር የማስተናገጃ ቤት አዘጋጅልኝ፤ በጸሎታችሁ ለእናንተ እንድሰጥ ተስፋ አደርጋለሁና። |
‘ጳውሎስ ሆይ! አትፍራ! በሮም ንጉሠ ነገሥት ፊት መቆም ይገባሃል! እነሆ፥ ከአንተ ጋር የሚጓዙትንም ሁሉ እግዚአብሔር ለአንተ ብሎ ከሞት ያድናቸዋል’ ብሎ ነግሮኛል።
ቀን ከቀጠሩለትም በኋላ ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያ ቤቱ መጡ፤ እርሱም ከጧት እስከ ማታ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በመመስከር አሳቡን ገለጠላቸው፤ እነርሱንም ለማሳመን ከሙሴ ሕግና ከነቢያት መጻሕፍት እየጠቀሰም ስለ ኢየሱስ አስረዳቸው።
ወደ እስፔን በምሄድበት ጊዜ እግረ መንገዴን ልጐበኛችሁ ዐቅጃለሁ። ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ደስ ብሎኝ ከቈየሁ በኋላ ጒዞዬን ለመቀጠል የሚያስችለኝን ርዳታ እንደምታደርጉልኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
እናንተም እኛን በጸሎት ልትረዱን ይገባል፤ በብዙ ጸሎት እኛ የእግዚአብሔርን ርዳታ ስናገኝ ብዙ ሰዎች ደግሞ በእኛ ምክንያት እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።
ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤
ልጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ነበረኝ፤ ነገር ግን ሁሉንም በደብዳቤ ልገልጸው አልፈልግም፤ ይልቅስ ደስታችን ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ መጥቼ ቃል በቃል ላነጋግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።