Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 27:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ‘ጳውሎስ ሆይ! አትፍራ! በሮም ንጉሠ ነገሥት ፊት መቆም ይገባሃል! እነሆ፥ ከአንተ ጋር የሚጓዙትንም ሁሉ እግዚአብሔር ለአንተ ብሎ ከሞት ያድናቸዋል’ ብሎ ነግሮኛል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ‘ጳውሎስ ሆይ፤ አትፍራ፤ በቄሳር ፊት መቆም ይገባሃል፤ ከአንተ ጋራ የሚጓዙትንም ሰዎች ሕይወት እግዚአብሔር አትርፎልሃል’ አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ጳውሎስ ሆይ! አትፍራ፤ በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ እነሆም፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር የሚሄዱትን ሁሉ ሰጥቶሃል፤” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፦ ‘ጳው​ሎስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቄ​ሣር ፊት ልት​ቆም ይገ​ባ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም ጋር የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሁሉ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ንተ ሰጥ​ቶ​ሃል።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 “ጳውሎስ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ እነሆም፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር የሚሄዱትን ሁሉ ሰጥቶሃል” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 27:24
35 Referencias Cruzadas  

ዘርህን አበዛዋለሁ፤ ታላቅ ሕዝብም ይሆናል፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎችም በረከት ትሆናለህ።


ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።


ሎጥ ይኖርባቸው የነበሩትን፥ በሸለቆ የሚገኙትን ከተሞች፥ እግዚአብሔር ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አስታወሰ፤ ስለዚህም ሎጥን ከጥፋት ወደሚድንበት ቦታ መራው።


ላባም “በልዩ መገለጥ እንደ ተረዳሁት በአንተ ምክንያት እግዚአብሔር የባረከኝ መሆኑን እንድገልጽልህ ፍቀድልኝ፤


እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ የሚያደርገው ነገር ሁሉ እንዲቃናለት ስላደረገ የእስር ቤቱ አዛዥ በዮሴፍ ቊጥጥር ሥር በነበረው ነገር ምንም ሐሳብ አልነበረበትም።


ይህም ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር በዮሴፍ ምክንያት የግብጻዊውን ሰው ቤት ንብረትና በውጪም በእርሻ ያለውን ሀብት ሁሉ ባረከለት።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ እግዚአብሔር ነኝ፤ ወደ ግብጽ ለመሄድ አትፍራ፤ እኔ ዘርህን በግብጽ አገር ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ፤


ኤልያስም እንዲህ አላት፤ “አይዞሽ አትጨነቂ! ሄደሽ ምግብሽን አዘጋጂ፤ አስቀድመሽ ግን ከዚያችው ካለችሽ ዱቄት ለእኔ ትንሽ እንጐቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ የቀረውንም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪው፤


ኤልሳዕም “አይዞህ አትፍራ፤ ከእነርሱ ጋር ከተሰለፈው ይልቅ ከእኛ ጋር የተሰለፈው ሠራዊት ይበልጣል” አለው።


ኃጢአት ብትሠራ የምትጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ነው፤ መልካም ሥራ ብትሠራ፥ የምትጠቅመው ሰውን ነው።


በጠራሁህ ጊዜ ወደ እኔ ቀርበህ “አትፍራ!” አልከኝ።


ከዚህ በኋላ ዳንኤል የባቢሎንን ጠቢባን እንዲገድል ከንጉሡ ትእዛዝ ወደተሰጠው ወደ አርዮክ ሄደና “የባቢሎንን ጠቢባን አትግደል፤ ይልቅስ ወደ ንጉሡ አቅርበኝና የሕልሙን ትርጒም ልንገረው” አለው።


ከሞት የተረፉትም የእስራኤል ሕዝብ በብዙ ሕዝቦች መካከል እግዚአብሔር እንደሚልከው ጠልና በሣር እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ፤ ተማምነው የሚጠባበቁት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ብቻ ይሆናል።


በእኔ ምክንያት፥ ወደ ገዢዎችና ወደ ነገሥታት ለፍርድ ስለምትወሰዱ በእነርሱና በአሕዛብ ፊት ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፤


ሥጋን ከመግደል አልፈው ነፍስን መግደል የማይችሉትን ሰዎች አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን አምላክ ፍሩ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በቀን ውስጥ ያለው ጊዜ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ የዚህን ዓለም ብርሃን ስለሚያይ አይሰናከልም።


ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ አስቦ “እዚያ ከደረስኩ በኋላ ወደ ሮም መሄድ አለብኝ” አለ።


በማግስቱ ሌሊት ጌታ በጳውሎስ አጠገብ ቆሞ “አይዞህ በኢየሩሳሌም እንደ መሰከርክልኝ፥ እንዲሁም በሮም ልትመሰክርልኝ ይገባሃል” አለው።


በደለኛ ከሆንኩ ወይም በሞት የሚያስቀጣ በደል ካደረግሁ ከሞት ልዳን አልልም፤ ነገር ግን የእነርሱ ክስ ከንቱ ከሆነ ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ አይችልም፤ እኔ ወደ ሮማ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ብዬአለሁ።”


በዚህ ጊዜ ጳውሎስ መቶ አለቃውንና ወታደሮቹን “እነዚህ መርከበኞች በመርከቡ ላይ ዐርፈው ካልተቀመጡ እናንተ ለመዳን አትችሉም” አላቸው።


በመርከቡ ውስጥ በጠቅላላው ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሰዎች ነበርን።


ከእስረኞቹ አንድ እንኳ ዋኝቶ እንዳያመልጥ ወታደሮቹ ሊገድሉአቸው አሰቡ።


የቀሩት ደግሞ በሳንቃዎችና በመርከቡ ስብርባሪዎች ላይ ሆነው እንዲወጡ አዘዘ፤ በዚህ ሁኔታ ሁሉም በደኅና ወደ ምድር ደረሱ።


ጌታም ሐናንያን እንዲህ አለው፦ “እርሱ ስሜን ለአረማውያን፥ ለነገሥታትና ለእስራኤል ሰዎች የሚያሳውቅ፥ የእኔ ምርጥ መሣሪያ ስለ ሆነ ወደ እርሱ ሂድ፤


በዚያውም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ሰምቶ ወደ እናንተ እንድመጣ እንደሚያደርገኝ ተስፋ ስላለኝ የማርፍበትን ቤት አዘጋጅልኝ።


ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤


ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅኩ፤ እርሱ ግን ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፤ “አትፍራ፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos