በሰይፋችሁ ትተማመናላችሁ፤ አጸያፊ ነገር ትፈጽማላችሁ፤ እያንዳንዱ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ዝሙት ይፈጽማል፤ ታዲያ፥ ምድሪቱ እንዴት የእኛ ርስት ናት ትላላችሁ?’
ዘኍል 5:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ሚስቱ በእርሱ ላይ እንዳመነዘረችበት ቢጠረጥርና ቅናት ቢያድርበት የሚፈጽመው የሕግ ሥርዓት የሚከተለው ነው፦ ይኸውም ሴትዮዋን በመሠዊያው ፊት ለፊት እንድትቆም ያደርግና ካህኑ ከላይ የተጠቀሰውን ሥርዓት ይፈጽምባታል፤ ወይም የቅናት መንፈስ በአንድ ሰው ላይ ቢያድርና ሚስቱን ቢጠራጠር ወደ መሠዊያው ፊት አምጥቶአት ካህኑ ይህን የሕግ ሥርዓት ይፈጽምባት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እንግዲህ የቅናት ሕግ ይህ ነው፤ አንዲት ሴት በትዳር ላይ እያለች ወደ ሌላ ሄዳ ከረከሰች፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሚስት በባልዋ ሥልጣን ሥር እያለች እርሱን ትታ ፈቀቅ በማለት ራስዋን በምታረክስ ጊዜ ያለው የቅንዓት ሕግ ይህ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በባልዋ ላይ ለበደለችና ራስዋን ላረከሰች ሴት የቅንዐት ሕግ ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴት ባልዋን ትታ በረከሰች ጊዜ፥ ወይም በሰው ላይ የቅንዓት መንፈስ በመጣበት ጊዜ፥ ስለ ሚስቱም በቀና ጊዜ፥ የቅንዓት ሕግ ይህ ነው፤ ሴቲቱንም በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፥ ካህኑም እንደዚህ ሕግ ሁሉ ያድርግባት። |
በሰይፋችሁ ትተማመናላችሁ፤ አጸያፊ ነገር ትፈጽማላችሁ፤ እያንዳንዱ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ዝሙት ይፈጽማል፤ ታዲያ፥ ምድሪቱ እንዴት የእኛ ርስት ናት ትላላችሁ?’
ይህ እንግዲህ ከበፍታም ሆነ ከበግ ጠጒር፥ ወይም ከቈዳ በተሠራ ልብስ ላይ በድሩም ሆነ በማጉ በሻጋታ አማካይነት የሚተላለፍ ምልክት ተመርምሮ የሚታወቅበት የሥርዓት መመሪያ ነው።
ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥ ስለ እርስዋ የሚፈልገውንም አንድ ኪሎ የገብስ ዱቄት ቊርባን ያምጣ፤ የቅናት ቊርባን ማለት በደልን የሚገልጥ የእህል ቊርባን ስለ ሆነ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አያድርግበት።
ከዚያም ካህኑ እንዲህ ብሎ ያስምላት፦ ከባልሽ ጋር እያለሽ ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር የተኛ ባይሆን፥ ራስሽንም ባታረክሺ ርግማን ከሚያመጣው ከዚህ መራራ ውሃ ነጻ ሁኚ።