Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 7:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ለእግዚአብሔር ስለሚቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ ‘አንድ ሰው ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሊከተለው የሚገባው ሥርዐት ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “ሰው ለጌታ የሚያቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 7:11
12 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ሕዝቅያስም ሕዝቡን “አሁን ራሳችሁን ለእግዚአብሔር የለያችሁ ስለ ሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ መሥዋዕታችሁን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አምጡ!” አላቸው፤ እነርሱም ንጉሡ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አንዳዶቹም በገዛ ፈቃዳቸው ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶችን አመጡ፤


የእግዚአብሔርንም መሠዊያ በማደስ በላዩ ላይ የኅብረት መሥዋዕትና የምስጋና መባን አቀረበ፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያመልኩም ዘንድ መላውን የይሁዳ ሕዝብ አዘዘ።


“እኔ መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ የስእለቴን መባ አቅርቤአለሁ፤


እንዲሁም ከእስራኤል የበግ መንጋዎች መካከል ከየሁለት መቶ በግ የተመደበው አንድ በግ ነው፤ ይህም ለእነርሱ የኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ከእህል ቊርባን ጋር የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ ነው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ሥጋውም እንስሳው በታረደበት ዕለት ወይም በማግስቱ መበላት አለበት፤ እስከ ሦስተኛው ቀን ተርፎ የቈየ ማናቸውም ሥጋ በእሳት ይቃጠል።


ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት በምታቀርብበት ጊዜ ተቀባይነት ታገኝ ዘንድ የመመሪያ ሥርዓቶችን ጠብቅ፤


በዘይት የተለወሰም ቢሆን ወይም ደረቅ ያልበሰለው የእህል መባ ግን ትውልዳቸው ከአሮን ወገን ለሆነው ካህናት ሁሉ ይሰጥ፤ እርሱንም እኩል ይካፈሉት።


“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፤ ማንም ሰው የአንድነት መሥዋዕት ቢያቀርብ ከእርሱ ከፍሎ ለእግዚአብሔር የተለየ መባ ያምጣ፤


የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል መባ ብታቀርቡልኝ እንኳ አልቀበላችሁም፤ ለደኅንነት መሥዋዕት ወደምታቀርቡልኝ የሰቡ ፍሪዳዎችም አልመለከትም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos