ቃሉም እንዲህ የሚል ነበር፦ “እኔ እግዚአብሔር ለይሁዳ ንጉሥ በተነበበለት መጽሐፍ ውስጥ በሚገኙት እርግማኖች ኢየሩሳሌምንና ሕዝብዋን ሁሉ እቀጣለሁ፤
ዘኍል 5:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህ በኋላ ካህኑ ይህን የእርግማን ቃል ይጽፈዋል፤ ጽሕፈቱንም አጥቦ የመራራ ውሃ ባለበት ዕቃ ውስጥ ይጨምረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ካህኑ እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ላይ ይጻፍ፤ በመራራውም ውሃ ይደምስሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ካህኑም እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ላይ ይጽፋቸዋል፥ በመራራውም ውኃ ያጠፋቸዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ካህኑም እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ላይ ይጽፋቸዋል፤ በመርገሙም መራራ ውኃ ይደመስሳቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ይጽፈዋል፥ በመራራውም ውኃ ይደመስሰዋል፤ |
ቃሉም እንዲህ የሚል ነበር፦ “እኔ እግዚአብሔር ለይሁዳ ንጉሥ በተነበበለት መጽሐፍ ውስጥ በሚገኙት እርግማኖች ኢየሩሳሌምንና ሕዝብዋን ሁሉ እቀጣለሁ፤
“ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ! መከላከያዬን አቀርባለሁ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ! ምነው ከሳሼም የክሱን ዝርዝር በጽሑፍ አቅርቦልኝ ባየሁት!
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው።
ይህም ሁሉ ሆኖ ኃጢአታችሁን ይቅር የምል አምላክ እኔ ነኝ፤ ይህንንም የማደርገው ስለ እናንተ ሳይሆን ስለ እኔነቴ ነው፤ ስለዚህ ኃጢአታችሁን አልቈጥርባችሁም።
ይህም ውሃ ወደ ሰውነትሽ ገብቶ ሆድሽን ያሳብጠው፤ ማሕፀንሽንም ያኰማትረው።’ ሴትዮዋም ‘አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ያድርግብኝ’ ብላ ትመልሳለች።
ታናናሾችንና ታላላቆችን ሙታን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ የሕይወት መጽሐፍ የሆነ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ ሙታንም በመጻሕፍቱ ተጽፎ በተገኘው ሥራቸው መሠረት ፍርድ ተቀበሉ፤