ከእነርሱም አንዳዶች ደግሞ ለሌሎቹ ንዋያተ ቅድሳት፥ ለዱቄቱ፥ ለወይን ጠጁ፥ ለወይራ ዘይቱ፥ ለዕጣንና ለልዩ ልዩ ቅመማቅመም ሁሉ ኀላፊዎች ነበሩ፤
ዘኍል 4:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በድንኳኑ ዙሪያ የሚገኘውን አደባባይ ምሰሶችን፥ እግሮቻቸውን፥ ካስማዎችን፥ አውታሮችንና ለእነዚህ ሁሉ መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ነው፤ እያንዳንዱም መሸከም ያለበትን ዕቃ በየስሙ ትመድብለታለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን ምሰሶዎች ከነመቆሚያ እግሮቻቸው፣ ካስማዎችን፣ ገመዶችን፣ ከእነዚሁ ጋራ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉና ማንኛውም ለአገልግሎቱ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። እያንዳንዱ ሰው የሚሸከመውን ዕቃ ለይታችሁ በስሙ መድቡለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዙሪያውም የሚቆሙትን የአደባባዩ ምሰሶች፥ እግሮቻቸውንም፥ ካስማዎቻቸውንም፥ አውታሮቻቸውንም፥ ዕቃዎቻቸውንና በተጓዳኝ የሚደረጉላቸውን አገልግሎቶች ሁሉ ነው፤ መሸከምም ያለባቸውን ዕቃዎች በየስሙ ትደለድላላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዙሪያውም የሚቆሙት የአደባባዩ ምሰሶዎች፥ እግሮቹም፥ የአደባባዩ ደጃፍ መጋረጃ ምሰሶዎች፥ እግሮቻቸውም፥ ካስማዎቹም፥ አውታሮቹም፥ ዕቃዎቹና ማገልገያዎቹ ሸክማቸው ነው፤ የሚጠብቁትንም የሸክማቸውን ዕቃ ሁሉ በየስማቸው ቍጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዙሪያውም የሚቆሙት የአደባባዩ ምሰሶች፥ እግሮቹም፥ ካስማዎቹም፥ አውታሮቹም፥ ዕቃዎቹና ማገልገያዎቹ ሸክማቸው ነው፤ የሚጠብቁትንም የሸክማቸውን ዕቃ ሁሉ በስማቸው ቍጠሩ። |
ከእነርሱም አንዳዶች ደግሞ ለሌሎቹ ንዋያተ ቅድሳት፥ ለዱቄቱ፥ ለወይን ጠጁ፥ ለወይራ ዘይቱ፥ ለዕጣንና ለልዩ ልዩ ቅመማቅመም ሁሉ ኀላፊዎች ነበሩ፤
የምሰሶዎቹ እግሮች የተሠሩት ከነሐስ ነበር፤ ኩላቦቹ ዘንጎቹና የምሰሶዎቹ ጫፎች መሸፈኛዎች ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ በብር ዘንጎች የተያያዙ ነበሩ፤
የእነርሱም ኀላፊነት በድንኳኑ ተራዳዎችና በመወርወሪያዎቻቸው፥ በምሰሶቹና ምሰሶቹ በሚቆሙባቸው እግሮች፥ እንዲሁም በሌሎች የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ሲሆን፥ በአጠቃላይ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት ሥራ ኀላፊነቱ የእነርሱ ነበር።
በዚህም ዐይነት እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተቈጠረ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እያንዳንዱ የማገልገልንና የመሸከምን ኀላፊነት ተቀበለ።
ሙሴ የመገናኛውን ድንኳን ተክሎ በፈጸመበት ቀን ድንኳኑንና የመገልገያ ዕቃዎቹን፥ መሠዊያውንና የመገልገያ ዕቃዎቹን፥ ዘይት በመቀባት ቀደሳቸው፤
ለሜራሪያውያን አራት ሠረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጠ። የእነርሱም አገልግሎት የሚከናወነው የአሮን ልጅ በሆነው በኢታማር ኀላፊነት ነበር።