ዘኍል 34:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደቡብ ድንበር ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምን ጠረፍ እያዋሰነ ያልፋል፤ ይኸውም በስተ ምሥራቅ በኩል የሚጀምረው ከሙት ባሕር በስተ ደቡብ ጫፍ ላይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የደቡብ ድንበራችሁ በኤዶም ወሰን ላይ ካለው ከጺን ምድረ በዳ ጥቂቱን ይጨምራል፤ በምሥራቅም በኩል የደቡብ ድንበራችሁ ከጨው ባሕር ጫፍ ይጀምርና መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደቡቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምያስን ዳርቻ እያዋሰነ የሚያልፈው ይሆናል፤ የደቡቡም ድንበራችሁ ከጨው ባሕር ዳር በምሥራቅ በኩል ይጀምራል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዜቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ በኤዶምያስ መያያዣ ይሆናል፤ የአዜብም ዳርቻ ከጨው ባሕር ዳር በምሥራቅ በኩል ይጀምራል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህች ናት፤ የደቡቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ በኤዶምያስ በኩል ይሆናል፤ የደቡቡም ዳርቻ ከጨው ባሕር ዳር በምሥራቅ በኩል ይጀምራል፤ |
የምድርህንም ወሰን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳው እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ እንዲሰፋ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁ፤ ከፊትህም ታሳድዳቸዋለህ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ በርስትነት የምታካፍላቸው የመሬት ድንበር የሚከተለው ነው፤ የዮሴፍ ነገድ ሁለት ድርሻ ይኖረዋል።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ውሃ በምድሪቱ ውስጥ ወደ ምሥራቅ፥ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆና ወደ ሙት ባሕር ይፈስሳል፤ ወደ ሙት ባሕር በሚፈስበት ጊዜ የጨዉ ባሕር ታድሶ ጥሩ ውሃ ይሆናል።
ድንበራችሁ በስተደቡብ ካለው ምድረ በዳ ተነሥቶ በስተሰሜን እስከሚገኙት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች ድረስ፥ በስተምሥራቅ ከትልቁ ወንዝ ከኤፍራጥስ፥ በመነሣት የሒታውያንን ምድር ሁሉ ጨምሮ በምዕራብ በኩል እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሆናል።
ውሃው መውረዱን አቆመ፤ በጻርታን አጠገብ አዳም ተብላ እስከምትጠራው ከተማ ድረስ ተከመረ፤ ወደ ሙት ባሕር ይፈስ የነበረውም ጐርፍ በፍጹም ተቋረጠ፤ ስለዚህም ሕዝቡ ወደ ማዶ ወደ ኢያሪኮ ተሻገሩ።