ዘኍል 33:56 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለበለዚያ እነርሱን ለማጥፋት እንዳቀድኩት ሁሉ እናንተን አጠፋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም በእነርሱ ላይ ለማድረግ ያሰብሁትን በእናንተ ላይ አደርግባችኋለሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በእነርሱ ላይ ለማድረግ ያሰብሁትን በእናንተ ላይ አደርግባችኋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም በእነርሱ አደርገው ዘንድ ያሰብሁትን በእናንተ አደርግባችኋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም በእነርሱ አደርገው ዘንድ ያሰብሁትን በእናንተ አደርግባችኋለሁ። |
በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ አሳዳችሁ ካላጠፋችሁ ግን ያስቀራችኋቸው ለዐይናችሁ እንደ ስንጥር ለጐናችሁም እንደ እሾኽ በመሆን ያስቸግሩአችኋል፤ በምትቀመጡባትም ምድር ዘወትር ጦርነት በማስነሣት ያስጨንቁአችኋል።
እግዚአብሔር እናንተን ለማበልጸግና ቊጥራችሁንም ለማብዛት እንደ ወደደው ሁሉ እንደገናም እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስ ደስ ይለዋል። ከዚህች ከምትወርሱአት ምድር ተነቃቅላችሁ ትጠፋላችሁ።
እግዚአብሔርም በብርቱ ተቈጣ፤ ከብርቱ ቊጣውም የተነሣ ከምድራቸው ነቃቅሎ ወደ ባዕድ አገር እንዲሰደዱ አደረጋቸው። ስለዚህም እነሆ፥ ዛሬም በዚያው ይገኛሉ።’