ዘኍል 32:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እኛ አገልጋዮችህ ለጦርነት የታጠቅን ሁሉ በእግዚአብሔር መሪነት ለመዋጋት ልክ አንተ ጌታችን እንደምታዘን ወደ ማዶ እንሻገራለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሮችህ ግን ልክ ጌታችን እንዳለው እያንዳንዱ ሰው ለጦርነት ዝግጁ ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት ለመዋጋት እንሻገራለን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሩ ግን እኛ ለጦርነት የተዘጋጀነው ባርያዎችህ ሁሉ በጌታ ፊት ጌታችን እንደ ተናገረ ወደ ጦርነት ለመዋጋት እንሻገራለን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ አገልጋዮችህ ግን ሁላችን የጦር መሣሪያችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ጌታችን እንደ ተናገረ ወደ ጦርነት እንሄዳለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ ባሪያዎችህ ግን ሁላችን ጋሻ ጦራችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ጌታችን እንደ ተናገረ ወደ ጦርነት እንሄዳለን። |
ከዚያም በኋላ ከወገኖቻችን ከእስራኤላውያን ጋር ወደ ጦርነት ለመሄድና የራሳቸው ወደሆነችው ምድር ገብተው እስኪሰፍሩ ድረስ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈን ለመዋጋት ዝግጁዎች እንሆናለን፤ እኛም ይህን ግዳጅ ፈጽመን እስከምንመለስ ልጆቻችን በእነዚህ በተመሸጉ ከተሞች ይኖራሉ፤ በዚህች ምድር ከሚኖሩትም ሰዎች ወገን ጒዳት አይደርስባቸውም።
“ምድሪቱን በዕጣ ለእስራኤል ሕዝብ እንድታከፋፍል እግዚአብሔር አንተን ጌታችንን አዞሃል፤ እንዲሁም የዘመዳችንን የጸሎፍሐድን ድርሻ ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አዞሃል፤